የጎዳና ህይወት
በሀገራችን ኢትዬጵያ በየቦታዉ ብዙ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ማየት የተለመደ ሆኖል ፡፡በአብዛኛዉ ህጻናት በሚጎዱበት በጎዳና ህይወት ላይ ይሄ ነዉ የሚባል ትኩረት ስላልተሰጠ ከእለት ወደ እለት የህጻናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ምን ያህል አሳሳቢ መሆኑን የሚያመለክት ጉዳይ ነዉ፡፡ በዚህ በአብዛኛዉ ትኩረት ባልተሰጠበት የጎዳና ህይወት ዙሪያ ተዘዋዉረን ባየንበት ወቅት ስላጋጠመን አንድ የህይወት ታሪክ በአጭሩ ልናገር፡፡ አካባቢዉ ጊዩርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሆን ከቤተክርስቲያኑን ግንብ ጋር ተያይዞ ከተቀዳደደ ላስቲክ አግድም ከተሰሩት መጠለያዎች መሀል ወደ አንዱ ጎራ አልኩ በመጠለያዉ አልጋነሽ ደስአለኝ ፣ ሀይማኖት ይልቃል እና የ 7ወር ልጅዋ በጋራ የኖሩበታል፡፡ አልጋነሽእድሜዋ 18 ሲሆን የመጣችዉ ከጎጃም ነዉ፡፡ ገና የ5ኛ ተማሪ ክፍል ተማሪ እያለች ማንነቱን የማታዉቀዉ አንድ ግለሰብ ወደ አዲስ አበባ ልዉሰድሽ ይላታል፡፡ እሳም አባተ ስለሞተና የምትኖረዉ ከችግረኛ እናትዋ ጋር በመሆኑ ምንም ሳታንገራግር እሺብላ ትከተለዋለች፡፡ እሱም በቀጥታ ወደ ጋምቤላ ወሰዳት ምንም ማድረግ ስለማትችል እዛዉ በጋምቤላ ክልል ጠጅ እና ስጋ እየሸጠች እሱን ማገልገል ጀመረች፡፡ ከዛም ወንዶች እያስቸገራት እዛ መስራት ስላልቻለች በ1ዓመት ከ6ወር 100ብር ብቻ በመያዝ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ እንደገባች ምንም መሄጃ ስላጣች እዛዉ ከመኪና የወረደችበት ቦታ ቁጭ ብላ ስታለቅስ አንድ ሰዉ መጥቶ ላሳድርሽ ብሎ ወስዶ እንደደፈራት እያዘነች አጫወተችኝ፡፡ከዛም በሃላ ተስፋ በመቁረጥ የጎዳናን ህይወት ተያያዘችዉ ለብዙም ወራት 50 ሣንቲም በመክፈል በላስቲክ ቤቶች ስታድር ከቆየች በሃላ አሁን ወደምትገኝበት ወደ ጊዩርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመምጣት ተጠግታ ትገኛለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት አልጋነሽ የሲጋራና የጫት ሱሰኛም ሆናለች፡፡ ከአልጋነሽ ጋር ተጠግታ የምትኖረዉ ሃይማኖትም የመጣችዉ ከጎጃም ነዉ ከአገርዋ የወጣችዉ ገና የ4ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት የ 18 ዓመት ልጅ ስትሆን የ 7 ወር ሴት ልጅም አላት ፡፡ የሚተዳደሩት በልመና ነዉ ከሁሉም የሚገርመዉ ግን የ 7 ወር ልጅ በቂ የልጅ እንክብካቤ ሳያገኝ እንዴት ሊያድግ እንደሚችል ነዉ፡፡ እናም ይሄ ታሪክ በመላዉ ኢትዮጵያ በብዛት እየታየ ነዉ ይህ ችግር ሊቀረፍ የሚችለዉ እንዴት እንደሆነ አሁንም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ፡፡ ህጻናትን እንንከባከብ፡፡












Post new comment