ዉሀ ጠማኝ
በርግጥ ባንባ ነኝ ስራዬም የሚመጣልኝን ዉሀ ለሰዉ ልጅ በንጽህና ማቅረብ ነዉ፡፡የዛሬን አያድርገዉና ህጻናት፣ጎልማሳዉ ሁሉም የሰዉ ፍጡር ባሰኘዉ ሰዓት እየመጣ ሲጠመዝዘኝ ሳልደብቅ የያስኩትን ሁሉ በንጽህና አቀርብለት ነበር፡፡ታዲያ የሰዉ ልጅ አስከፋኝ በዉሀ ጥምም ገደለኝ በአግባቡ የዉሀ ጥያቄዉን ማቅረብ ሲገባዉ በመጣና በሄደ ቁጥር ጆሮዬን ሲጠመዝዝ ለብልሽት ተጋልጬጫኀን ማየት ተስኖኛል፡፡ ስለዚህ ሰዎች እባካችሁ እኔ አንዴ አካለ ስንኩል ሆኜ ቀርቻለሁ ነገም የወንድማቼ እጣ ፋንታ ይሄ እንዳይሆን የምትጠቀሙበትን እቃ በእንክብካቤ ያዙት፡፡












Post new comment